Facebook Page: Please enter a valid URL

ሐዋሳ፣መጋቢት 1/2018 ዓ.ም፦ የሲዳማ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን (ማርች 8)ን በድምቀት አክብረዋል።

“ማርች 8″ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ50ኛ ጊዜ ”የሴቶች ድምጽ እኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።

በበአሉ አከባበር ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ሰለሞን እንደተናገሩት የመደመር መንግስታችን ለሴቶች እኩልነትና ነጻነት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ጠቅሰዉ የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲጎለብት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ሴቶች ለራሳቸውም ሆነ ለሀገራቸው ለውጥና እድገት ተግተው መስራት እንሚጠበቅባቸው ገልጸው የሴቶችን መብት ለማረጋገጥ በቆራጥነት መታገልና አሁን ላይ ዓለም የደረሰበትን የዕድገትና ልህቀት ፍጥነት ልክ ራሳቸውን በማብቃት ተሳትፎአቸወንና የውሳኔ ሰጭነት ሚናቸዉን ሊያሳድጉ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሴቶች በተሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ ብቁ እና ተወዳዳሪ በመሆን የዚህን ዘመን የራሳቸውን ታሪክ ለማጻፍ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በዓሉን አስመልቶ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 አከባበር፣ ይዘትና አጀማመር ላይ ያተኮረ ሰነድ ለውይይት መነሻነት ቀርቧል።

በቀረበው ሰነድ መነሻነት የበዓሉን አከባበር ሂደትና የሴቶች ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ያለበት አበረታች ደረጃን ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማስተሳሰር ሰፋ ያለ ውይይት በተሳታፊዎች ተደርጓል።

Posted in: City News

Leave a comment